በድሬዳዋ አስተዳደር የተከሰተውን የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታወቀ

    በድሬዳዋ አስተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተውን የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታውቋል። የጤና ቢሮው በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ቺኩንጉንያ የተባለው የበሽታ ምልክት እስካሁን በ3 ሺህ 756 ሰዎች ላይ ተስተውሏል። ሆኖም ግን በሽታው ከወባ እና ከደንጌ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው ሁሉም ታማሚዎች ቺኩንጉንያ በተባለው በሽታ ስለመያዛቸው ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋገጠም ነው ቢሮው ያስታወቀው። የድሬዳዋ አስተዳደር…

    Read More

      በዘንድሮ የክረምት በጎፍቃድ ስራ የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት ጨምሯል

      በ2011 ዓ.ም የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት መጨመሩ ተገለፀ፡፡ በክረምት የዕረፍት ወቅት የተለያዩ የበጎፍቃድ አገልግሎቶችን ለመስጠት የህብረተሰቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመቀነስ ዓላማን አንግቦ እየተካሄደ ባለው የ2011 ዓ.ም የክረምት የበጎፍቃድ አገልግሎት በተለይ በትምህርት እና ስልጠና በጎፍቃድ ስራ የወጣቶች ተሳትፎና ተነሳሽነት መጨመሩ ታውቋል፡፡ እንደ አስተዳደር በርካታ ወጣቶች እየተሳተፉበት ያለው የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት ከተለያዩ የበጎፍቃድ ስራዎች…

      Read More

        የባከኑ የህዝብና የመንግስት ሃብቶችን ማስመለስና አጥፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ይገባል ተባለ

        የባከኑ የመንግስትና የህዝብ ሃብቶችን ማስመለስና አጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት አሳሰቡ፡፡ ለገጠሩ ህዝብ ፍትህን ተደራሽ የማድረግ ሥራም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ነው የተገለፀው፡፡ የአስተዳደሩ ምክር ቤት 42ተኛ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤ በአስተዳደሩ የዋና ኦዲተር ጽ/ቤት፤ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት፤ የብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ፣ በአስተዳደሩ የመጀመሪያ ደረጃና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች…

        Read More

          የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ለአዲሱ በጀት ዓመት ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ አጸደቀ

          የአስተዳደሩ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባኤ ከ2 ቢሊዮን 8 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ እና ወ/ሮ ከሪማ አሊን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ተጠናቅቋል፡፡ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የሥራ አጥነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም የድሬዳዋ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ ለሁለት ቀናት የተካሄደው 2ተኛ የሥራ ዘመን 42ኛው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባኤ ሲጠናቀቅ የድሬዳዋ…

          Read More

            “የድሬዳዋን የፍቅርና የአንድነት መግለጫ እሴቶች ለመመለስ መረባረብ ይገባል” የድሬዳዋ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ

            ለሀገር አርአያ የሆነውን የድሬዳዋን የፍቅር፣ የሰላምና የአንድነት መገለጫ እሴቶች ለመመለስና ሀገር አቀፉን ለውጥ ከዳር ለማድረስ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አንድ ዕድል ለሰላም›› በሚል መሪ ሃሳብ በተኪያሄደው የዛፍ ጥላ ሥር የእርቅ ውይይት ላይ ሀገር አቀፍ ታላቅ ስብዕና የተላበሱ የሀገሪቱ የኪነ ጥበብና የዘርፈ ብዙ ሙያተኞች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት…

            Read More