ለችግሮቻችን ባለቤት እና አድራሻ ልናበጅላቸው ይገባል
የመልካም አስተዳደር ችግሮችም አንበላቸው ሌሎች ችግሮች የአስተዳደራችን አሊያም የሀገራችን ችግር የሚሆኑት ትንንሽ የምንላቸው ችግሮች እየተደመሩ ሲሄዱ ነው፡፡ ችግሮች ደግሞ እየተደመሩ የሚሄዱት ትክክለኛ አድራሻቸው ባለመታወቁ ነው አለበለዚያም ለችግሮቹ ያለን ግምት የተሳሳተ ከመሆኑ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚሁ ጋራ ተያይዞ ችግሮቻችንን በባለቤትነት ስሜት ለመፍታት ያለመንቀሳቀስ በራሱ እንደ አንድ ችግር አድራሻና ባለቤት ሊፈለግለት ይገባል፡፡ የትኛውም ችግር ያራሱ አድራሻ እና…


