ሉካንዳ ቤቶች የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታ አሰሙ መንግስት በበኩሉ ነፃ ገበያ ብንከተልም ህዝብ ሲመዘበር ዝም አንልም ብሏል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጲያ የምትከተለው ነፃ ገበያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሆኑን ተከትሎ ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ውጪ ባሉት እቃዎች ላይ መንግስት የዋጋ ተመን ማስቀመጥ እንደማይችል ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህንን መብት በመጠቀም አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የህዝብን ኢኮኖሚ ሲያቃውሱ እየተስተዋለ ነው፡፡ ከፋሲካ በአል ጀምሮ በተለያዩ የአስተዳደሩ አካባቢዎች በሚገኙ ሉካንዳ ቤቶች የ1 ኪሎ የከብት ስጋ ዋጋ እስከ 360 ብር…


