የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ ፈተናውን ያለምንም የፀጥታ ችግር ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡ አዳዲስ የኩረጃ ዘዴዎችም ከወዲሁ ከሽፈዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ እንዲሁም ክልላዊ ፈተናዎች ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ት/ቢሮ ከድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽንና ከድሬዳዋ አስተዳደር መምህራን ማህበር ጋር በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት ያለፉት አመታት ተሞክሮዎችን በመውሰድ በዘንድሮው አመት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተመጣጠነ የጋራ እቅድ በማዘጋጀት…


