ትውልድ ተሸጋሪ አጀንዳዎችን እናስብ፤ እንተግብር
ይህች ዓለማችን በርካታ ሀሳቦች በተለያዩ የድምጽ ቃናዎች ታጅበው እዚህም እዚያም የሚደመጡባት ናት፡፡ ከእነዚህ አስተሳሰቦች መሀል በቁጣ ድምጽና በመሳሪያ ታጅበው ሳንፈልጋቸውና ሳናምንባቸው እንድንቀበላቸው የሚያስገድዱ ናቸው፡፡እነዚህ አስተሳሰቦች የዜጎችን መብቶች ለመጣስና ነጻነትንና ዴሞክራሲን ለማጥፋት እንደተነሱ ገና ከአነሳሳቸው የሚያስታወቁ ናቸው፡፡ ሌሎቹ አስተሳሰቦች ደግሞ በማባበያ ቃላትና በበሬ ወለደ የፈጠራ ወሬ የታጀቡ ሲሆን የዋሆችን የማሳመን አቅማቸው ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ብዙዎችን ስሜታዊ…


