‹‹ህግ የማስከበር ስራ ላይ ባለስልጣን መ/ቤቱና ግብር ከፋዩ ተቀራርቦ መስራት ይጠበቅበታል›› አቶ ካሊድ መሀመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የሉካንዳ ንግድ ዘርፍ ግብር አወሳሰን እና አሰባሰብ ሥርዓትን ለመወሰን አዲስ በወጣው የአፈፃፀም መመሪያ ማሻሻያ ላይ ከግብር ከፋዮች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀደም ብሎ በስራ ላይ የነበረውን መመሪያ ቁጥር 8/2009 ያሉበትን ክፍተቶች በማጥናት በመመሪያ ቁጥር 18/2011 ማሻሻሉንም አስታውቋል፡፡ ይህ የሉካንዳ ንግድ ዘርፍ ግብር አወሳሰን እና አሰባሰብ ሥርዓትን ለመወሰን የተሻሻለው አዲሱ መመሪያ በግብር ሰብሳቢው ተቋምና በግብር ከፋዩ ህብረተሰብ መካከል ቀደም ብሎ ለአሰራር የሚያስቸግሩ አንቀፆችን በመለየት ማስተካከል የተቻለ ሲሆን ይህም የነበሩትን የአሰራር ችግሮች እንደሚቀርፍ በመድረኩ ላይ…


