What Is the Average American Income in 2021?

    Contents Types of Averages Median Salary by State Household size Average Salary In US per Month 【Latest 2022】 | CareerExplorer Average Wealth For Asian Americans Therefore, a good salary is certainly higher when compared to the average salary in America. Because of this, it is yet again important for us to apply the median formulas…

    Read More

      ህዝበ ክርስትያኑና ህዝበ ሙስሊሙ የመከባበርና የመፈቃቀር ባህላቸውን በድምቀት በሚከበረው የጥምቀት በዓል ማሳየት እንዳለባቸው ተገለፀ ፡፡

      የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ ጣሀ እንደገለፁት የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ከመሆኑም ባሻገር በዩኔስኮ በአለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ በዓል መሆኑን ተናግረዋል፡፡  ይህ ደማቅ በዓል በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ከሐይማኖት አባቶች፣ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይት መደረጉንም ገልፀዋል፡፡   ድሬዳዋ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ተከባብረውና ተፈቃቅረው…

      Read More

        በአስተዳደሩ ውስጥ ለሚገኙ 82 የኃይማኖት ተቋማት ለሚያስተዳድሯቸው የቤተ-እምነት ስፍራዎች ህጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ

        በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ 9 የኦርቶዶክስ አቢያተክርስቲያናት፣ 66 የሚስሊም መስጊዶች እና 7 የፕሮቴስታንት አቢያተክርስቲያናት በአጠቃላይ 82 የሀይማኖት ተቋማት የመሬት ይዞት ማረጋገጫ ካርታ ከአስተዳደሩ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ተረክበዋል፡፡ በካርታ ርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋን ጨምሮ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ መሬት…

        Read More

          ብስክሌትን የትራንስፖርት አማራጭ የማድረግ ባህል እንዲዳብር ጥሪ ቀረበ ከ55 ዓመታት በላይ የክስ ሪከርድ የሌለባቸው አሽከርካሪዎች ተሸልመዋል፡፡

          ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 22/2012 መንገድ ላይ የሚደርስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ታስቦ ሲካሄድ የቆየው የንቅናቄ ፕሮግራም ማሣረጊያውን የከተማዋን ስራ ፈላጊ ወጣቶች ብስክሌት በመሸለምና ለበርካታ አመታት ምንም አደጋ ሳያደርሱ ህግን ባለመተላለፍ ላሽከረከሩ ሹፌሮች የሜዳሊያና የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት ማሣረጊያውን አድርጓል፡፡ ህብረተሰቡም ብስክሌትን እንደ አማራጭ ትራንስፖርት በመጠቀም የትራፊክ መጨናነቅን እንዲቀንስ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ አስተዳደር…

          Read More

            “በህብር ወደ ብልፅግና” የምሁራን የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

            ምሁራን ቀደም ሲል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎና በመንግስትም የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚደረገው ጥረት አጥጋቢ አልነበረም፡፡ ይሁንና ይህን ሰፊ ክፍተት የተረዳው መንግስት ክፍተቱን ለመሙላት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም ይህን አገራዊ ክፍተት በመረዳትና የምሁራንን አይነተኛ ሚና በመገንዘብ ምሁራንን ያሳተፈ “በህብር ወደ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከምሁራን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች…

            Read More

              ባለፉት 3 ወራት የ14 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ጠፍቷል ባሳለፍነው አመት በመንገድ ላይ በሚፈፀም የትራፊክ አደጋ7 መቶ 44 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል 31 ዜጎች ህይወታቸው አለፋል ይህ አደጋ እያስከተለ ያለው ጉዳት እያሻቀበ መሆኑን ማሳያው ደግሞ አሁንም በአስተዳደሩ ባለፉት 3 ወራት ብቻ የ14 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ማለፉ ነው፡፡

              በሀገር አቀፍ ደረጃ የትራፊክ አደጋ የንቅናቄ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚረዱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ከታህሳስ 07 እስከ 22/2012 ዓ.ም የሚቆይ የንቅናቄ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስሜነህ ለማ የትራፊክ አደጋን አስመልክቶ በተናገሩት ንግግር በአለማችን ካሉት መኪኖች 100%…

              Read More

                የድሬዳዋ አስተዳደር ከቻይናው ሲ.ሲ.ኢ.ሲ.ሲ ጋር የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ስምምነት ተፈራረመ

                የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከቻይናው ሲሲ.ኢ.ሲሲ (CCECC) ኩባንያ ጋር የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱንም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ ቡህ እና የሲሲ.ኢ.ሲሲ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጉዎ ቾንግፌንግ ትናንት በድሬዳዋ ከተማ ተፈራርመዋል። በትናንትናው እለት የተፈረመው ስምምነት በከተማዋ የቻይናው ሲሲ.ኢ.ሲሲ (CCECC) በመጀመሪያ ዙር በ370 ሄክታር መሬት ላይ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት የሚያስችለው መሆኑን የድሬደዋ ከንቲባ ዕህፈት…

                Read More

                  ለመጪው ትውልድ ምቹ ድሬዳዋን ለማስረከብ በአካባቢ ጥበቃ ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ተባለ፡፡

                  የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደን እና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ለአስተዳደሩ ነዋሪ የአካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ግንዛቤ ለመጨመር ያለመ አስተዳደራዊ ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡ ‹‹ያልተገራ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም የመጪውን ትውልድ ህልውና የሚጋፋ ተግባር ነው››በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ኮንፍረንስ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት ድሬዳዋ በተፈጥሮ አደጋ መጠቃቷ የቅርብ ጊዜ ትውስታ መሆኑን…

                  Read More

                    የኢትዮጵያ ኦ/ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ በድሬዳዋ ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰጠቱ ለአስተዳደሩ ምስጋና አቀረቡ።

                    በድሬዳዋ መሐል ከዚራ በሚገኘው ሚካኤል ቤተከርስቲያን በተዘጋጀው የምስጋና መርሀግብር ላይ የተገኙት ብፁእ አቡነ ማትያስ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኗን የዘመናት ጥያቄ ተቀብሎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመስጠቱ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ቤተከርስቲያኗ ለምትሰጠው አገልግሎት ድጋፍና ትብብር ላበረከቱ ተቋማትም የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል። በምስጋና መርሀግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አህመድ ቡህ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ በቅርስነት በመመዝገቡ የተሰማቸውን ደስታ…

                    Read More

                      “በህብር ወደ ብልፅግና” የምሁራን የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

                      በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምሁራን ቀደም ሲል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎና በመንግስትም የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚደረገው ጥረት አጥጋቢ አልነበረም፡፡ ይሁንና ይህን ሰፊ ክፍተት የተረዳው መንግስት ክፍተቱን ለመሙላት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም ይህን አገራዊ ክፍተት በመረዳትና የምሁራንን አይነተኛ ሚና በመገንዘብ ምሁራንን ያሳተፈ “በህብር ወደ ብልፅግና” በሚል መሪ…

                      Read More