የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው ከተላኩት የ8 ሰዎች ናሙና ውስጥ 4ቱ ከበሽታው ነፃ መሆናቸው ተገልፆል።
የ4ቱ ውጤት ገና ያልመጣ ሲሆን ይህንንም ውጤት እንዳወቀ የሚገልፅ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል።
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም በሽታው በአስተዳደራችን ሲከሰትም ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
የለይቶ ማቆያና የህክምና ማዕከል በድሬዳዋ ጤና ጣቢያ (ነምበር ዋን) የተዘጋጀ ሲሆን ከሰሞኑም የምድር ባቡር ሆስፒታልን(ፈረንሳይ ሆስፒታል) ለዚሁ ስራ መረከቡ ይታወቃል
ሆስፒታሉን በህክምና ቁሳቁስ የማሟላት ስራ እየተሰራ ነው።
ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋርም በመሆን የግንዛቤ ስራዎችም እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በአስተዳደሩ ብሎም በሀገር ደረጃ የተከሰተውን የሳኒታይዘር ችግር ለመቅረፍም ከጤና ጥበቃ የተላከውን 1300 ሊትር አልኮል ከሌሎች አስፈላጊ ውህዶች ጋር በመቀላቀል ለጤና ተቋማት እያከፋፈለ ይገኛል።
ከጤና ተቋማት በመቀጠልም ከስራቸው ጋር በተያያዘ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ተቋማት ይሰጣል።
በቀጣይም በምናገኘው ግብዓት ልክ ክፍፍሉ የሚቀጥል ይሆናል።
ህብረተሰቡ የተቻለውን ጥንቃቄ ሁሉ በማድረግ ራሱንና ማህበረሰቡን እንዲጠብቅና በተለያዩ ህጋዊ ተቋማት የሚቀርቡ መረጃዎችን በመተግበር ሀላፊነቱን እንዲወጣ ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል።
ምንጭ :- ድሬደዋ ጤና ቢሮ


