አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ በድሬደዋ ሳባ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ በድምቀት ምንም አይነት የፀጥታ ችግርም ሆነ የወንጀል ተግባር ሳይፈፀምና የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት በሰላም መከበሩን ፖሊስ ገለፀ::
ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት እገዛና ትብብር ላደረጉ ሁሉ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል:: በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታልቅ ድምቀት በታህሳስና ሀምሌ ወር የሚከበረው አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ በድሬደዋ የእምነቱ ተከታዩች በተገኙበት በዛሬው እለት በድምቀት ሲከበር ምንም አይነት የፀጥታና የወንጀል ተግባር ሳይፈፀምና የትራፊክ አደጋ ሳይደርስ ተከብሯል ሲል ነው የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው:: ከቁልቢ በአለ ንግስ ጋር ተያይዞም በርካታ ቁጥር…


