ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት እገዛና ትብብር ላደረጉ ሁሉ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል::
በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታልቅ ድምቀት በታህሳስና ሀምሌ ወር የሚከበረው አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ በድሬደዋ የእምነቱ ተከታዩች በተገኙበት በዛሬው እለት በድምቀት ሲከበር ምንም አይነት የፀጥታና የወንጀል ተግባር ሳይፈፀምና የትራፊክ አደጋ ሳይደርስ ተከብሯል ሲል ነው የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው::
ከቁልቢ በአለ ንግስ ጋር ተያይዞም በርካታ ቁጥር ያለው ምእመንና ተሽከርካሪ ባለፉት ቀናት ወደ ከተማዋ እንደመጡ የገለፀው ፖሊስ ምእመናኑ በከተማው ምንም አይነት የወንጀል ተግባርና የፀጥታ ችግር እንዲሁም የትራፊክ አደጋ ሳያጋጥማቸው የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው በአሉ ወደ ሚከበርበት ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በሰላም አምርተዋል ብሏል ::
ፖሊስ ኮሚሽኑ አይይዞም እንደገለፀው ከበአለ ንግሱ ጋር ተያይዞ የነበሩ ጥንቃቄዎችና የህብረተሰብ አጋርነት በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖበታል ያለ ሲሆን ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት እገዛና ትብብር ሲያደርግ ለነበረው የበአሉ አክባሪ ምእመን እንዲሁም ሁሌም ለሰላሙ ቀድሚያ ለሚሰጠውና ሚናው ከሁሉ ለሚልቀው የአስተዳደሩ ነዋሪ ለመከላኪያ ሰራዊት ፣ለፌደራል ፖሊስንና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና ተቋማት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል::
ምንጭ ድሬ ፖሊስ


