የአስተደደሩ ነዋሪዎች በ ሀሰት ፕሮፖጋንዳ መረበሽ እንደሌለበት ተገለፀ።

    የድሬደዋ ከንቲባ ከድር ጆሀርና የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ ከቁልቢ ገብርኤል በአል አከባበር ጋር ተያይዞ ያለውን የፀጥታ ጉዳይና በአስተዳደሩ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በሰጡት መግለጫ የድሬዳዋ ህብረተሰብ ወደ ከተማችን የቁልቢ ገብሬል የንግስ በአልና የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ሀገራዊ ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ዲያስፖራዋችን በድሬደዋዊ ፍቅር በመቀበል ወደ ቀደመው የፍቅር፤ የመቻቻል ከተማችንን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የጁንታው ተላላኪ የሆኑ በበሬ ወለደ ወሬ ሳንደናገር ሰላማችንን ማስጠበቅ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
    የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሙሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው እንደገለፁት ከቁልቢ ገብርኤል ከንግስ በአሉ ጋር ተያይዞ በአሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እና የትራፊክ አደጋ እንዲከበር ለማስቻል ከኦሮሚያ ፖሊስ ፤ ሀረር ፖሊስ ፤ ፌደራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት የጋራ እቅድ በማውጣት ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል ፡፡
    በአሉን ለማክበር ወደ ድሬዳዋ የሚመጡ እንግዶች ቀደም ብለው የሚገቡ በመሆኑ በከተማዋ ውስጥ የሚያደርጉት ቆይታም ሰላማዊ እንዲሆን የቅድመ ስራዋች መጠናቀቁን ኮሚሽነር አለሙ ገልፀዋል ፡፡
    ኮሚሽነር አለሙ በድሬዳዋ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በመግለጫቸው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱ ወሬዎች ከእውነት የራቁ እንደሆኑና በተለይ የከተማዋ ሁሉም ቀበሌዎች ፍፁም ሰላማዊ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የተመታው የኦነግ ሸኔ ቡድን ራሱን ለማሸሽ ወደ ድሬዳዋ ገጠር ቀበሌ ወደሆነችው የቢዮ አዋሌ ክላስተር መታየቱን ነው የተናገሩት፡፡
    ከእዚሁ ጋር ተያይዞ የፀጥታ አካሉ እስከ ህይወት መስዋእትነት ጭምር በመክፈል ባደረገው ጠንካራ ኦፕሬሽን የተማረኩ እና የተመቱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት እንዳሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል ፡፡
    ኬሚሽነር አለሙ ለአስተደደሩ ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክትም በውሸት ፕሮፖጋንዳ ሳይሸበሩ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸችሀል ብለዋል ፡፡
    የከተማዋ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ባለንብረቶች የብሔር ብሔረሰቦች በዕል በሰላም እንዲጠናቀቅ ያደረጉትን አስተዋፆኦ በመድገም ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች የትራንስፖርት ክፍያ በአግባቡ በመቀበል የጁንታው ተላላኪዋች የከተማዋን ገፅታ ለማጥፋት እያደረጉት ያለውን የሽብር ወሬ በማጋለጥና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኬሚሽነር አለሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።