የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በዘንድሮ በጀት አመት “የተፋሰስ ልማት ለሌማት ቱሩፋት” በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ በነበረው ስልጠና መጠቃለያ ላይ የስራ አቅጣጫዎችን ሊከናወኑ በሚገባ ተግባራት ላይ መልክት አስተላለፉ።
ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በመልክታቸው እንደገለጹት የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በላቀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማከናወን የሞት ሽረት ጉዳይ እንደሆነ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ስራዎች የተገኙ ውጤቶች በቂ ማሳያ እንደሆኑ አመላክቷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዘንድሮ በጀት አመት “የተፋሰስ ልማት ለሌማት ቱሩፋት” በሚል መሪ ቃል ለምናከናውነው ተግባር ላለፉት ሁለት ቀናት በተዘጋጀው የእቅድ ውይይት ላይ በቂ ግንዛቤ እንደገኛችሁና በመተማመን የተቀናጀ…


