ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በመልክታቸው እንደገለጹት የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በላቀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማከናወን የሞት ሽረት ጉዳይ እንደሆነ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ስራዎች የተገኙ ውጤቶች በቂ ማሳያ እንደሆኑ አመላክቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዘንድሮ በጀት አመት “የተፋሰስ ልማት ለሌማት ቱሩፋት” በሚል መሪ ቃል ለምናከናውነው ተግባር ላለፉት ሁለት ቀናት በተዘጋጀው የእቅድ ውይይት ላይ በቂ ግንዛቤ እንደገኛችሁና በመተማመን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን ያስገኙትን ጠቀሜታዎች በቅጡ በመረዳት ዘንድሮ በሚከናወኑ ስራዎችን በቁርጠኝነት ለማከናወን ያላችሁ ከፍተኛ ተነሳሽነት በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


