በዚሁ መደበኛ ጉባኤ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 3ተኛ አመት 7ተኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎች ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 2ተኛ አመት 6 ተኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 2ተኛ አመት 2ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ በምክር ቤቱ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላት እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ 2016 ዓ.ም የ 6 ወር ሪፖርት ሪፖርትም የሚቀርብ ይሆናል ።
መደበኛ ጉባኤው በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ( ረቂቅ ) አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ በስተመጨረሻም የተለያዩ ሹመቶች የሚኖሩም ይሆናል ።
በዚሁ ጉባኤ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ\ሮ ፈቲህያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ የምክር ቤት አባላት ፣ ቋሚ ኮሚቴዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል ።


