ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ
መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በፆም፣ በፀሎትና በስግደት የሚከበረው ፀሎተ ሀሙስ በዛሬው ዕለትም በድሬዳዋ ቅድስት ማሪያም ካቴደራል ቤተክርስትያን በተለያዩ ስነ-ስርአቶች ተከብሯል ። በዚህም ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሀዋርያቱን እግር በማጠብ ትህትናውን የገለፀበትን ተግባር በማሰብ “ህጽበተ እግር” ተከናውኗል። በፀሎተ ሀሙስ እየሱስ ክርስቶስ ታላቅ መንፈሳዊ ሚስጥርን የገለጠበት በፀሎት መትጋትንና ትህትናን በተግባር ያስተማረበት እንደሆነም ቀሲስ ደበበ ተመስገን ተናግራዋል። በአሉን…


