የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ሲገኝ የመደመር ትውልድ የቤተ መፅሀፍት ግንባታ ፕሮጀክት የስራ ሂደትንም ተመልክተዋል።
በዚህም ቤተ-መፅሀፍቱ ዘመናዊ በሆነ መልኩ በጥራትና በፍጥነት የግንባታ ሂደቱን እያከናወነ ሲገኝ ሲጠናቀቅም ለዩኒቨርስቲ፣ ለ ቲቪኢቲ፣ ለሀይስኩል እንዲሁም ከኤለመንተሪ/ የመጀመሪያ ደረጃ/ ተማሪዎች በተጨማሪም ለሪሰርቸሮችና / ለጥናትና ምርምር ሰሪዎች/ በአጠቃላይ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።
ቤተ-መፅሀፍቱ ዲጂታልና ዘመናዊ ከመሆኑ ባሻገር ለአካል ጉዳተኛ ወገኖች ምቹ ሲሆን የህፃናት መዋያም እንደሚኖረው በመስክ ምልከታው ተገልፃል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ


