በአሁኑ ሰአት በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት በመገኘት በወረዳው በ6 ወራት የተሰሩ የልማትና የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርትን እያደመጡ ይገኛሉ።
በዚህም በሪፖርቱ በስራ እድል ፈጠራ፣ በንግድ ዘርፍ፣ ዲጂታል ድሬን በማፋጠኑ ረገድ፣ በወረዳ ደረጃ ገቢን በመጨመር እንዲሁም በሌማት ቱሩፋት ማለትም በእንቁላል፣ በማርና በወተት ምርት እንዲሁም በከተማ ግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል።
በአጠቃላይ ከመድረኩ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በቀጣይም በወረዳው የተሰሩ ስራዎች ላይ የመስክ ጉብኝት የሚደረግ ይሆናል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ


