ብስክሌትን የትራንስፖርት አማራጭ የማድረግ ባህል እንዲዳብር ጥሪ ቀረበ ከ55 ዓመታት በላይ የክስ ሪከርድ የሌለባቸው አሽከርካሪዎች ተሸልመዋል፡፡
ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 22/2012 መንገድ ላይ የሚደርስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ታስቦ ሲካሄድ የቆየው የንቅናቄ ፕሮግራም ማሣረጊያውን የከተማዋን ስራ ፈላጊ ወጣቶች ብስክሌት በመሸለምና ለበርካታ አመታት ምንም አደጋ ሳያደርሱ ህግን ባለመተላለፍ ላሽከረከሩ ሹፌሮች የሜዳሊያና የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት ማሣረጊያውን አድርጓል፡፡ ህብረተሰቡም ብስክሌትን እንደ አማራጭ ትራንስፖርት በመጠቀም የትራፊክ መጨናነቅን እንዲቀንስ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ አስተዳደር…


