የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ዲስትሪክት ለ7ኛ ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ ባለእድለኞችን ሸልሟል፡፡
በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ያለው የቁጠባ ባህል እንዲጎለብት በተለያዩ መንገዶች በሰራሁት ስራ ከ1.2 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት አስችሎኛል አለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ዲስትሪክ፡፡ ባንኩ የ7ኛው ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ ባለእድለኞችን ሸልሟል፡፡ ወጣት ናትናኤል ሁነኛው በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን ከእለት ገቢው ላይ በቆጠባት አነስተኛ ገንዘብ በደረሰው እጣ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ተሸላሚ ሆኗል ወጣቱ…


