የኢፌድሪ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከድሬዳዋ አስተዳደር ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

    የኢፌድሪ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን በድሬዳዋ የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ማለትም መስከረም 12 -2013 ባካሄደዉ የጋራ የምክክር መድረክ ላይ በአስተዳደሩ በ2013 በጀት አመት ከ23 ሺ በላይ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንና ከዚህም ዉስጥ ወደ ስራ የገባዉ የድሬ ደዋ ኢንዲስቲሪ ፓርክ ይገቡ የነበሩ የተለያዩ ኩባኒያዎች በዓለም ላይ በተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ሚክኒያት በመዘግየታቸዉ እና በበጀት አመቱ ባርካታ ኩባኒያዎች የሚገቡ በመሆኑ በኢንዲስቲሪ ፓርኩ እስከ 10ሺ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል እና ለኩባኒያዎቹ የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብ እና አገልግሎቶችን የሚሰጡ የተለያዩ የስራ መስኮችን የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፆዋል፡፡
    በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የፌዴራል ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነርአቶ ኑጉሱ ጥላሁን በድሬዳዋ የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አደረጃጀቱን የማሻሻል ስራ በማከናወን በተሻለ የስራ ዕድል ፈጠራ የማመቻቸቱን ስራ ማከናወን እንዳለበት ጠቁመዋለ፡፡
    በመድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ እና በምክትል ከንቲባ ማዓረግ የነግድ ኢንደስቲሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከዲር ጁሃር እንዲሁም በአስተዳደሩ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡