በድሬ ደዋ በተካሄደ ድንገተኛ ኦፕሬሽን የተለየዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ በቁጥጥር መዋሉ ተገለፀ::

    በድሬ ደዋ የጋራ የሰላም ም/ቤት ባካሄደዉ ድንገተኛ ኦፕሬሽን የተለየዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ በቁጥጥር መዋሉን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንደስቲሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከዲር ጁሃር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጨያ ገለፁ፡፡
    በድሬዳዋ አስተዳደር የተለየዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ እና ከህገወጥ የገንዘብ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከ944 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ተይዘዋል::
    በቁጥጥር ስር ከዋለዉ የተለየዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ መካከል 8 ሺ 611 የአሜሪካ ዶላር ፣ 1 ሺ 250 የካናዳ ዶላር ፣ 165 የሳዉዲ አረቢያ ሪያል እንዲሁም የአዉሮፓ ህብረት መገበያያ የሆነዉ 745 ዩሮ በቁጥጥር ስር ከዋለዉ የተለየዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ መካከል መሆኑንም አብራርተዋል