ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ በምክክር መድረክ ላይ እንደተናገሩት የፀጥታ አካላት ተገቢውን ግንዛቤ በመውሰድ ከገንዘብ ኖት ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በመቆጣጠር ሂደት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና አብራርተዋል፡፡
የፀጥታ አካላቱ በክልላቸው እና በከተማ አስተዳደር ተጨማሪ ኬላዎችን በማቋቋም ስራዎችን መሰረት እንዳለባቸው የገለፀት ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ እነዚህን ስራዎች ለማከናወን የፀጥታ አካላት በቂ ግንዛቤ ይዘዉ ስራዎችን ሊያከውኑ እደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው ሁሉም የፀጥታ አካላት ቁርጠኛ ሆነዉ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ጠቅሰው አመራሩ በሚገባ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት በድሬዳዋ ከተማ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝዉዉርን ለመግታት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዉ ይህ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ ላይ የፀጥታ አካላቱ በዋናነት ሊሰሯቸው የሚገባ ተግባራት የተገለፀ ሲሆን የፀረ ሰላም እንቅስቃሴን መስበር ፤ሙሰኞች እና ኮትሮባንድስቶች መግታት፤ እና ፍትሀዊ የገንዘብ ዝውውር በመፍጠር ቀን ከሌት መስራት እንዳለበት ተብራርቷል ፡፡
ህገ -ወጥ ገንዘብን በመያዝ ወደ ባንክ እንዳይገባ በመከላከል ሀገርን የማዳን ስራ መስራት እንዳለበት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ ገልፀው ለሰከንድ ችላ ማለት እንደማይገባ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል ፡፡


