የመስቀል ደመራ በዓል ኮሮና ቫይረስን ታሳቢ ባደረገ መንገድ በድምቀት እንደሚከበር ተገለፀ
ህዝበ ክርስቲያኑ በአሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማስታወስ ሊሆን ይገባል ተብሏል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪሃጅ ሊቀትጉሃን ማቲያስ በቀለ በሰጡት መግለጫ የደመራ በአል በተለመደው ሃይማኖታዊ ስርዓት እንደሚከበር ገልፀዋል።
በዓሉ በርካታ ምዕመን አንደማሳተፉ ኮሮናን ታሳቢ ያደረገ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሊቀ ትጉሃን አሳስበዋል።አያይዘውም ይህ ታላቅ በዓል ያለምንም እንከን አንዲከበር ታዳሚው ሃይማኖታዊ ስረዓቱን ብቻ ተከትሎ ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል ሊቀ ትጉሃን።
በመጨረሻም በአሉን ስናከብር ለሐገራችን ሰላምና አንድነት በጋራ የመንቆምበት የተቸገሩ ወገኖችን አያሰብን ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ።


