በድሬዳዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።

    የኢፌድሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ በተገኙበት የተካሄደውን የውይይት መድረክ ከንቲባ አህመድ ቡህ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ አስጀምረዋል ።
    በድሬዳዋ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ጋር በተደረገው በዚህ የጋራ የውይይት መድረክ ዶ/ር አብረሃም በላይ የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራምንና አጠቃላይ የትግል ስልቱን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
    የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይና
    በብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም ላይ ያተኮሩ አስተያየትና ጥያቄዎችን በስፋት አንስተዋል::
    ለተነሱት አስተያየትና ጥያቄዎችም ዶ/ር አብረሃም በላይ እና የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኅላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
    ድሬዳዋ ከንቲባ ፅ/ቤት
    መስከረም 28/ 2013 ዓ.ም