የፖሊዬ ክትባት ዘመቻ በድሬደዋ አስተዳደር እና በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል::

    የክትባት ዘመቻው ሲጀመር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቤሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ፣ የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
    ከዛሬ መስከረም 27 – 30 ድረስ ለተከታታይ 4 ቀናት የሚቆየው ይህ የፖሊዬ ክትባት ዘመቻ በ4 ክልሎች ማለትም (ደቡብ/ብ/ብ/ህ/፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በሐረሪ) እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች (አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ) እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ 7 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
    ሁሉም ህብረተሰብ ይህን በመገንዘብ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸውን ቤት ለቤት በሚመጡ የጤና ባለሞያዎች እንዲያስከትብ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡