ለመንግስት አገልግሎት ዘርፍ በተዘጋጀው የ15 አመት ፍኖተ ካርታና የ10 አመት መሪ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ ።
“የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ ተደራሽ ፣ ገለልተኛና ሙያዊ ሲቪል ሰርቪስ እንገነባለን”!በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደውን ውይይት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመተባበር ያዘጋጁት ነው ።
የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ ቡህ እና
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ ባደረጉት ንግግር በተጀመረው የውይይት መድረክ ላይ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ የመንግስት አገልግሎት እስከአሁን ሲመራበት ከነበረው በተለየ ሁኔታ ዜጋ ተኮር ይዘት ባለው የ15 አመት ፍኖተ ካርታና የ10 አመት መሪ እቅድ ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ ሰጥተዋል።
ገለፃውን ተከትሎ በተወያዮች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ኮሚሽነር በዛብህና ምክትላቸው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
በውይይት መድረኩ ላይ ም/ከንቲባ ከድር ጁሀርና ም/አፈጉባኤ አብዱሰላም አህመድን ጨምሮ የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እንዲሁም የመንግሥትና የፓርቲ የስራ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ድሬዳዋ ከንቲባ ፅ/ቤት
መስከረም 28/2013 ዓ.ም


