ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ሁለተኛውን ዙር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ቀን የፊታችን እሁድ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በድማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በተለይም የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማበረታታት፤የብስክሌት ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማሳደግና አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ለማጎልበት ፤እግረኞችን ለማበረታታት ነው ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በዚህም በ2012 ዓ.ም የጸደቀውን የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
እሁድ ጥቅምት 1/ 2013 ዓ/ም ማለዳ በሚካሄደውና መነሻውን ከድሬደዋ ምድር ባቡር በፈረንሳይ ሆስፒታል መዳረሻውን በምድር ባቡር አደባባይ ያደረገ የብስክሌት ፤የእግር ጉዞና የተለያዩ ትርኢቶች እንደሚኖሩ ጠቅሰው ህብረተሰቡም በዚህ በርካታ ጥቅም ባለው ፕሮግራም እንዲሳተፉ ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡


