በድሬዳዋ አስተዳደር በተሻሻለው የመሬት ካሳ አዋጅ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ::

    ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ መንግስት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሮአቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወይም ሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው ብለዋል።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባው ጽ/ቤት የልማት ተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ መልሶ መቋቋም እና ቀሬታ አፈታት አዲሱ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለከፍተኛ የፓርቲና የተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳተፈዋል።
    በስልጠና መድረኩ አዲስ የወጣው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 እና የካሳ ደንብ ቁጥር 472/2012 ግልጽ በሆነ መልኩ ለተሳታፊዎች ቀርቧል።
    በቀረበው ሰነድ ሰፊና ወሳኝ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ሰነድ አቅራቢዎች ዘርዘር ያለ ምላሽ ሰጥተውበታል።
    በስልጠናው ማጠቃለያ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የመሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብዙዓለም አድማሱ የመሬት ካሳ ጉዳይ በህግና በህግ ብቻ መመለስ ስላለባቸው አመራሩና ባለሙያዎች አዋጅና ደንቡን በአግባቡ ተረድተው ወደ ስራ በመግባት በአተገባበሩ ጠንካራ ክትትል ድጋፍ በማድረግ መቀናጀት እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል።
    በመጨረሻም ም/ከንቲባው ለአዋጁና ለደንቡ አተገባበር ጠንካራ ተቋም በማቋቋም እንዲሁም መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን በመግለጽ መድረኩ ተጠናቀቀ።
    ጥቅምት 10/2013 ዓ.ም
    ምንጭ ከ ብልፅግና ፓርቲ