በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በቀጣይ ቢሮው ከቀበሌዋችና ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት አብሮ የመስራቱን አጠናክሮ ከመቀጠል አንፃር፣ ባለፉት አመታት በዘርፉ የታዪ ችግሮችን ከመቅረፍ ፣የሴክተርና የቀበሌ የሰው ኃይል ማሟላትና የሚዲያና የኮሙዪኒኬሽን ዘርፍ መደበላለቅ ቢጠራ እንዲሁም የመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ የቋንቋ ብዛህነት በኮሙዪኒኬሽን ዘርፍ ሊሻሻሉ ይገባል ሲሉ አንስተዋል።
በተነሱት ሀሳቦች ላይ ምላሽ የሰጡት በአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ አካላትን ማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል እንዳለ እንደተናገሩት በአስተዳደሩ የምትታተመው የመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ የቋንቋ ስብጥር እንዲኖራት በሱማሌኛና በኦሮምኛ ቋንቋ ለማስጀመር አደረጃጀቱ ተጀምሯል በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጀመራል በማለት በሴክተርና በቀበሌዋች የሰው ኃይልን የሟሟላት እና በቅንጅት አብሮ መስራቱ ቀደም ካሉት አመታት በተሻለ መልኩ በተጠናከረ መልኩ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ሂደቶች ይኖሩናል ብለዋል።
አቶ ሚካኤል አክለውም ለዘርፍ ባለድርሻዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት የበጎ ገፅታ መገንባትና የጋራ መግባባት እንዲፈጠር የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በውይይቱም በኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲሁም የሰው ሀይል እጥረትና በቀጣይ ጊዜያት በእቅድ ዘመኑ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶች ላይ በስፉት ተወያይተዋል።
በትዕግስት ቶሎሳ


