በድሬዳዋ አስተዳደር ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት ተጀመረ፡፡

    በአለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ላለፉት 7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለትበ በ8 ኛ እና በ 12 ክፍል ተማሪዎች ተጀመረ፡፡
    በዛሬው እለትም በአስተዳደሩ በሚገኙ የከተማና ገጠር ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሲጀመር የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በየትምህርት ቤቶቹ ተዟዙረው ትምህርት ከማስጀመር በተጨማሪ ለተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ አበርክተዋል፡፡
    በኮሮና ቨይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየ የመማር ማስተማር ሂደት በ2013 የትምህርት ዘመን እንዲጀመር አስተዳደሩ በትምህርት ቤቶች የኬሚካል ርጭት እንደተደረገ የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ተማሪዎች አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በየመማሪያ ክፍሎቹ ከ 20 እስከ 25 ወንበሮችን በማስገባት በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራቱን ተናግረው፡፡ ከኒትባው ከዚህም ጋር በማያያዝ በቀጣይ የጤና ባለሞያዎችን ወደ ትምህርት ቤቶቹ በመላክ የኮሮና ምርመራ ናሙና እንዲወሰድ ከማድረግ አንስቶ ትምህርት ቤቶቹም የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታን በምን አግባብ እየተከላከሉ እንደሚገኝ ክትትል በማድረግ የትምህርት ሂደቱ እንዲቀጥል እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ ባለሀብቶችና የመንግስት ተቋማትን በማስተባበር የተገኘውን የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን ለትምህርት ቤቶች መሰራጨቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ተናግረዋል፡፡
    ከረጅም ወራት ቆይታ በኋላ ትምህርት በመጀመሩ መደሰታቸውን በከተማዋ የሚገኙ ተማሪዎች ተናግረው በትምህርት ቤት ቆይታቸውም የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታን ለመከላከል የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡም ነው የተናገሩት፡፡