ቋሚ ኮሚቴው የ1ኛ ሩብ አመት የመስክ ምልከታውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት የመስክ ምልከታቸውን የጀመሩት በኢንዱስትሪ መንደር በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ባለቤትነት የወጣቱን የስራ እጦት እንደሚያቃልል ታምኖበት በመገንባት ላይ የሚገኘውን የብረታ ብረትና እንጨት ማምረቻ ወርክሾፕ የግንባታ ሂደት በመመልከት ነበር ፡፡
በወቅቱም በቁጥር ስድስት የሆኑት ወርክሾፖች በ29 ሚሊየን ብር ወጪ በመገንባት ላይ እንደሚገኙና ተጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡም ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድልን እንደሚፈጥሩ በሳይት ተቆጣጣሪው ኢንጅነር ጆኒ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በቋሚ ኮሚቴው ምልከታ ወቅት የቅያሪ ቦታ ሳይሰጠን ከመስሪያ ቦታችን የመፈናቀል ስጋት አለን ያሉ ወጣቶች ቅሬታ ሲያቀርቡ የኮርፖሬሽኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ በሀር አሜ በበኩላቸው ወጣቶቹ ለወርክሾፕ ግንባታው ቦታውን ሲለቁ ምትክ ቦታ ተሰቷቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በቦታው ላይ ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው በማምረት ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን እንቅስቃሴ የቃኘው ቋሚ ኮሚቴው ከማምረቻ ቦታ ማስፋፊያ ጋር ተያይዞ በይዞታ ይገባኛል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለው ችግር እንዲፈታም በኮርፕሬሽኑ ለቋሚ ኮሚቴው የቀረበ ቅሬታም ነበር፡፡
ሌላው በቋሚኮሚቴው ምልከታ የተደረገበት በአስተዳደሩ ከ47 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ተገንብቶ ያለአገልግሎት የተቀመጠውናለውድመት እየተዳረገ ያለው የተርንኪ ፕሮጀክት ሲሆን በምልከታውም የመንግስት ሀብት ለውድመት በመዳረግ ላይ እንዳለ ለመመልከት ተችሏል፡፡
በ01ቀበሌ የሚገኘው የማምረቻና መሸጫ ቦታ፤ለገሀሬ ማምረቻና መሸጫ፤መጋላ ማምረቻና መሸጫ፤ ቦታዎች እንዲሁም ጫት ተራ የሚገኘው የማምረቻና መሸጫ ቦታ ላይ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ሆሉም ቦታዎች በታሰበላቸው ፍጥነት አለመጠናቀቃቸውንና ፈጥነው ተጠናቀው ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በፍትሀዊነት ሊተላለፉ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቱው በምልከታው ወቅት ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽ ግብረመልስ ሰቷል፡፡ የኮርፖሬሽኑአመራሮችና ባለሙያዎችም የዘገዩትን አጠናቆና ያሉትን ችግሮች ለይቶ ፈጥነው ለስራ አጥ ወጣቶች ለማስተላለፍ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይ ቀን ውሎው የሲቪክ ማእከልና ቴክኒክና ሙያ ማስፋፊያ ግንባታ ሂደትን ተመልክቶ ግብረመልስ ሰቷል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ አይናለም ተዘራም የምልከታው ዋና አላማ በመስክ ያሉ ችግሮችን በመመልከት ግብረመልስ መስጠትና የህዝብና መንግስት ሀብት ባግባቡ ስራ ላይ መዋሉን መቆጣጠር ነው ብለዋል፡፡ምልከታው በቀጣይ ቀናትም ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡


