በድሬደዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ተጠናቀቀ::

    በድሬደዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
    በሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች ተነስተው ው ይይት የተደረገባቸው ሲሆን በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ ተሰጦባቸዋል፡፡
    መድረኩን የመሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ታግለው መብታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል ያሉ ሲሆን ለሌሎች ሳይሆን ለውድ አገራችን እጣ ፋንታ ስንል የምንታገለውን አካል በትክክል አውቀን መታገል ያስፈልጋል ይህ ባይሆን ግን እንዳሁኑ ዋጋ ያስከፍለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    በመጨረሻም በድሬደዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲያዘጋጅ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተመርጧል፡፡