በአለም አቀፍ ደረጃ ለ19 ጊዜ በሀገራችን ለ18 ጊዜ ”ሙስናን መታገል በተግባር ”በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ ገቢዋች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በዓሉን በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡
የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ከተቋሙ ከስራ ባህሪ በመነሳት ተቋሙ ለሙስና ተጋላጭነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ይህን ለመቀነስ በጥሩ ስነ-ምግባር አሰራርን በመዘርጋት የግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን በደንበኞች እርካታና ፍታዊነትን ተደራሽነትን በማስፋት የመስራት ልምድ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
የባለስልጣን መ/ቤቱ የስነ ምግባር መኮንን አቶ መሐዲ ዘኮ የሙስና ባሕርያት ፤ መገለጫዎች መንስሔዎችና ምክንያቶችን በማንሳት የመታገያ ስልት ፤ የጸረ ሙስና የሕግ ማሕቀፎችና በኢትዮጵያ የጸረ ሙስና ትግልና እንቅስቃሴ በዝርዝር የያዘ ሰነድ አቅርበዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይም የገቢዋች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብዱሰላም መሐመድ እና ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መርየን መሐመድ አወያይነት የባለስልጣኑ ባለሙያዋች አጽዕኖት በመስጠት ተወያይተዋል::
በመድረኩም ቀጣይ ተቋሙ ትኩረት ሰቶ በሚንቀሳቀስባቸው አቅጣጫዋችን የተወያዩ ሲሆን ሙስናን የመከላከያ ስልቶች በማቅረብ አመራሩና ሰራተኛውና ሰፊ ውይይት አድርገዋል።


