እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

    በክርስቲያኖች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የዕርቅ መጀመሪያ ተደርጎ ይታሰባል። ከልደቱ በፊት በፈጣሪና በፍጡር፣ በሰማይና በምድር፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ታላቅ የጠብ ግድግዳ ተገንብቶ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። የልደት በዓል “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለው የፈጣሪ ቃል በተግባር መፈጸም የጀመረበት፤ በአምላክና በሰው ልጆች መካከል ዕርቅ የተወጠነባት ዕለት ናት። ይህ በዓል መለያየት የጠፋበት፣ ኅብረትና አንድነት የጸናበት፤ መለኮትና ሥጋ፣…

    Read More

    የምወዳችሁና የማከብራችሁ ክርስቲያን ወገኖቼ፤ የገናን በዓል #እንዴት ለማክበር አሰባችሁ❓

    ሁሌም በዓል ሲደርስ ከቤተሰብና ከወዳጅ ዘመድ ጋር በህብረት ማክበር የብዙዎቻችን ፍላጎትና ደስታ ነው። ልክ እንደ እኛ ይሄ ፍላጎት ኖሯቸው… በበዓል ቀን ህዝባቸውን ለማገልገል ሲሉ በፀጥታና ደህንነት፣ በህክምና፣ በትራንስፖርት፣ በሚዲያ እና ሌሎች ስራዎች ላይ የሚያሳልፉ ወገኖቻችን በርካታ ናቸው። በአቅማችን የበዓል ስጦታ ይዘን፤ ብቻቸውን እንዳልሆኑ፣ ለአገልግሎታቸውም ልዩ ክብርና ምስጋና እንዳለን ብንገልፅላቸው፤ የሚያገኙት ደስታ ልዩ እንደሚሆን አምናለሁ። ለሰላምና…

    Read More

      የሃይማኖት አባቶች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

      የሃይማኖት አባቶቹ የ2015 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ በመልዕክታቸውም÷ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የፍቅር እና የትህትና መሠረት በመሆኑ ክርስቲያን ምዕመኑ ርስበርስ በመፋቀር እና በመዋደድ በተግባር ሊተረጉመው ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ወደዚች ምድር መምጣቱ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ማሳያ በመሆኑ እኛም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያሳየውን ፍቅር ማሳየት…

      Read More

        የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የቄራ አገልግሎትን ድርጅትን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ስር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኘ።

        የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ በዛሬው የሶስተኛ ቀን ውሎው የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የቄራ አገልግሎትን ድርጅትን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ስር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተመልክተዋል። ምልከታውም ግብረመልስ አተገባበርን በተመለከተ፣ በህዝብ ውክልና መድረክ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥን…

        Read More