የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የቄራ አገልግሎትን ድርጅትን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ስር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኘ።

    የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ በዛሬው የሶስተኛ ቀን ውሎው የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የቄራ አገልግሎትን ድርጅትን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ስር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተመልክተዋል።
    ምልከታውም ግብረመልስ አተገባበርን በተመለከተ፣ በህዝብ ውክልና መድረክ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥን እንዲሁም የ2015 አ.ም የዝግጅት ምእራፍ አፈፃፀምን በተመለከተ እንደሆነ ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ ገልፀዋል።
    በዚህም በከተማ ውስጥ ያለውን የቄራ አገልግሎት የተሳለጠ ለማድረግ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን አዲሱን ቄራ ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችሉ የጀላባና የውሃ አገልገሎቶች እንዲሟሉለት አቅጣጫ በተቀመጠለት መሰረት ይህን ከማሟላት አንፃር ምን እየሰራ እንደሚገኝ ቋሚ ኮሚቴዎቹ ጎብኝተዋል።
    በዚህም አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ወ/ሮ አንድነት ገልፀዋል።
    ከፍተኛ ችግር ሆኖ የቆየውን የጀላባ ቦታ ማግኘት ላይም ሂደቶች እንደተጀመሩ ወ/ሮ አንድነት አንስተው ግንባታውንም ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑን ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ ጥናት መደረጉንና ይህንንም ወደ ስራ ማስገባት እስኪቻል ድረስ ጀሎ አካባቢ የሚገኘውን ውሃ ፕሪዘርቫየር ገንብቶ መጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች በሂደት ላይ እንደሆኑ ቋሚ ኮሚቴው ተመልክቷል።
    በትላንትናው ዕለት ቋሚ ኮሚቴው በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ምልከታ ያደረገ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ በመልካ ተቆፍረው ወደ ስራ ያልገቡ የውሃ ጉድጓዶችን ወደ መስመር ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተመልክተዋል። በተለይም የሲቪክ ወርክ ስራውን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ ግብአቶችም ተገዝተው የገቡበት ሁኔታ እንዳለ እንዲሁም የተለያዩ የውሃ ጉድጓዶችን መቆፈራቸውን ቋሚ ኮሚቴው የጎበኘ ሲሆን ይህ ስራም ተጠናቆ ውሃውን ወደ መስመር ማስገባት ከተቻለ የከተማዋን የውሃ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀርፍው ወ/ሮ አንድነት ገልፀዋል።
    ቋሚ ኮሚቴው በከሰዓት ውሎው የድሬዳዋ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ስር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ማለትም በክረምት በጎ ፍቃድ ለአረጋውያን የተሰሩ ቤቶችን አይተዋል። እንዲሁም ደግሞ የነርሰሪ ሳይትን የጎበኙ ሲሆን በዚህ ሳይትም ከሌማት ትሩፋት ጋር ተያይዞ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን እንደተመለከቱ ወ/ሮ አንድነት ተናግረዋል። በቦታው ላይ የሚስተዋለውን የውሃ እጥረት እንዲፈታ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።