የአስተዳደሩ የሲቪክ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ የውል ስምምነት ተፈጸመ፡፡

    በአስተዳደሩ ባለ ብዙ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ የሆነው የሲቪክ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ከቻይናው CCECC ጋር የሳይት የውል ስምምነት ርክክብ ተደረገ፡፡
    ስምምነቱም በዋናነት የሲቪክ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት የኢንቴሪየር ዲዛይን ቀሪ ስራዎችን ለመጨረስ በአስተዳደሩ በክብር ምክትል ከንቲባ የውል ስምመነት መፈረሙን ተከትሎ በስምምነቱ መሰረት የሳይት ርክክብ በዛሬው እለት ከቻይናው CCECC ጋር የሳይት የውል ስምምነት ርክክብ መደረጉን የድሬደዋ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ጸ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ አስተውቀዋል፡፡
    ፕሮጀክቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅም የ14 ወራት ጊዜ ገደብ የተሰጠ ሲሆን ተቋራጭ ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ባለው ልምድ እና በሚጠቀማቸው የዘመኑ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በተያዘለት ጊዜ በጥራት ገንብቶ እንዲያስረክብም ነው ሀላፊው ያሳሰቡት፡፡
    የሲቪክ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት ተሰርቶ ሲጠናቀቅም ለአስተዳደሩ ነዋሪ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ገልጸው በውስጡ ከ2000 ሺ በላይ ታዳሚን የሚይዝ የስብሰባ አዳራሽ ፣ለቲያተር ለፊልም የሚውሉ አዳራሾችን፣የአርት ጋለሪ፣ሙዚየም ፣ ቤተ መጸሀፍት፣ ጥናትና ምርምርን የሚያደርጉ ማዕከላት እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ካፍቴሪያዎች የሚይዝ መሆኑን ሀላፊው አቶ ሚካኤል እንዳለ አስረድተዋል፡፡