በንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ውስጥ በመሳተፍ በአገር ዕድገት ላይ የድርሻውን ለማበርከት አላማ ያለው የአለ ቀሎ የንግድና የኢንቨስትመንት አክስዮን ማህበር ዛሬ በድሬዳዋ በቢካፒታል ሆቴል ተመሠረተ ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጁሃር በምስረታው ስነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስት ሁሉም ሰው በማህበር ተደራጅተው በአገር ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የድርሻቸውን ለማበርከት የሚያደርጉት ጥረት እንድምያበረታታ ገልፀው አላ ቀሎ ማህበረ ከዚህ በፊት በውጪ አገር ብደራጁም በአገራቸውም ባላቸዉ ሀብት በንግድና እንቨስትመንት ስራ ላይ በመሳተፍ ከእራሳቸው አልፈው ወገኖቻቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ የምያደርጉትን ጥረት አስተዳደሩ እንደምያበረታታ ገልፁዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሃም ዩሱፍ በበኩላቸው አገራዊ የለውጥ ሂደቱን ተከትሎ እንደ አገርና እንደ ድሬዳዋ ባለሃብቶች በሚፈለጉት የስራ ዘርፍ ተሰማርተው ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታዎች እንደተፈጠረ ገልፁው አክስዮን ማህበሩ በአካባቢው ፤ በአገሪቱና በተለያዩ የውጭ አገራት የሚገኙ አባላቶቹን በማሰባሰብ በድሬዳዋና በአገር ደረጃ የተሻሉ ስራዎች ለመስራት የሰነቀው አላማ እንዲሳካ በየደረጃው የሚገኘው የመንግስት መዋቅርና አመራር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል ።
አላ ቀሎ የምለው ለስያሜው ተጠቀምን እንጂ ሁሉም ሰው ሼሩን በመግዛት የማህበሩ አባል መሆን ይችላል ያሉት የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀረር መሀመድ ማህበሩ በውጭ አገር በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መቋቋሙንና የወገኖቻቸውን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሲሳተፉ እንደነበረ ጠቅሰው ይህንን ማህበር ወደ” አለ ቀሎ ንግድና ኢንቨስትመንት አክስዮን ማህበር” በማሳደግ በልማትና በንግድ ተግባራት ላይ ለመንቀሳቀስ ስምምነት በመፍጠር ወደ ተግባር መሸጋገራቸውንም እብራርተዋል ።
የማህበሩ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መሀመድ ፋራህ በበኩላቸው ማህበሩ ከ22.2 ሚሊዮን ብር በላይ ተቋቁመው ወደ ስራ እንደገባና በአገሪቱ በተፈጠረው ልውጥና ሰላም እንዲሁም ምቹ የስራ ሁኔታን በመጠቀም ወገኖቻችንም ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ብሏል።
በዕለቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ነዋሪዎች ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች፣ ሃደስንቄ ና ታዋቂ ግለሰቦችና እንዲሁም የተለያዩ ባንኮች ተጠሪዋች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።


