የድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ አለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን ደረጃ በማሟላት በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከ ዩጋንዳ አቻው ጋር የሚያደርገውን የወዳጅነት አለም አቀፍ ጨዋታውን በማስተናገድ ላይ ነው።
የድሬዳዋ ስቴዲየም ወደ ቀደሞ ክብር እና ዝና ለመመለስም አስተዳደሩ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ የስቴዲየሙን የማስፋፊያ እና እድሳት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን በዛሬው እለትም የእግር ኳስ ሜዳ የሳር ንጣፍ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ተመርቋል።
ታሪክን በመድገም የድሬዳዋ ስታዲየምን የቀድሞ ገጽታዋን በማልበስ በኩል ከፍተኛ አሻራቸውን ያኖሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ስቴዲየም አለም አቀፍ ጫወታዎችን በሚያስተናግደው መርሀ ግብር ላይ በመገኝታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አለም አቀፍ ስቴዲየም ከሀገር ውጪ ለሚደረጉ ጫወታዎች በገንዘብ በአቅም የሚወጣውን ወጪ በማስቀረት በኩል አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የድሬዳዋ አለም አቀፍ ስቴዲየም 25ሺህ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል ።


