መላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ የሁለት ወራት የጾም፥ ፀሎትና ስግደት ጊዜ አጠናቃችሁ፥ ለናፈቃችሁት የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም እና በጤና ስለደረሳችሁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።
በዓሉን ስታከብሩ… እውነተኛ ፍቅር ካለን አንዳችን ለሌላኛው መስዋዕት በመሆን የወደቁትን ማንሳት፥ የተራቡትን ማብላት፥ ያዘኑትን ማፅናናት እንደምንችል እና ከበርካታ ልዩነቶቻችን ይልቅ ሰብዓዊ አንድነታችን እንደሚበልጥ በመገንዘብ ሊሆን ይገባል።
በቀጣይ እያንዳንዳችን ብዝሀነታችንን በአገራዊ አንድነት በማጠንከር፥ የሁላችን ኢትዮጵያን ከድህነት ክፉ ጨለማ – ወደ ብልፅግና ብርሀን በማሸጋገር ሂደት ውስጥ፥ የራሳችንን ድርሻ እና ኅላፊነት በአግባቡ እንድንወጣ ወንድማዊ መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ። መልካም በዓል!


