የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ተረትና ምሳሌ የያዘው “ማክማክሳ” መፅሀፍ ተመረቀ

3 ሺ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ተረትና ምሳሌ የያዘው “ማክማክሳ” የተሰኘ መፅሀፍ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በመድረኩ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ መፅሀፉ ለተማሪዎች እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ እንደሚጠቅም ገልፀዋል።

አቶ ኢብራሂም አያይዘውም እንደነዚህ አይነት ባህልና ወግን ለትውልድ የማስተላለፍ ስራ ላይ በመሰማራታቸው የመፅሀፉን አዘጋጅ አመስግነዋል።

የመፅሀፍ ፀሀፊ የድሬዳዋ ተወላጅና ለበርካታ አመታት በባህር ማዶ የኖሩት ኢንጂነር አብደላ ሼክ መሀመድ በበኩላቸው ለዛሬ ቀን በመድረሳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

መፅሀፉ 331 ገፆች ያሉት ሲሆን የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተረትና ምሳሌዎች በቅደም ተከተል ተዘርዝረው እንደሰፈሩበት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *