የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር ባሉ አብያተ ቤተክርስትያናት በልዩ ሁኔታ ተከበረ

የስቅለት በዓል ድሬዳዋ በመንበረ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ካቴድራል ሲከበር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በቤተክርስትያኑ በመገኘት ጣፉጭ ምግቦችን ፣ዳቦ እና ውሀ በማቅረብ የስቅለት በአልን አክብረው ለሚወጡ ምዕመናን ብርታትና ጥንካሬን ተመኝተዋል።

በተመሳሳይ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ምክትል ከንቲባ. እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣የብልፅግና ፖርታ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣የብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዩ በመገኘት ለህዝበ ክርስትያኑ ያላቸውን ፍቅር በመግለፅ አብሮነታቸውን እና አጋርነታቸውን አሳይተዋል

በአስተዳደሩ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስትያናት የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሰላምና አብሮነት በዓሉ ተከብሯል

ምዕመኑም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች ወንድም እህቶቻቸው ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ሁለት የፆም ወራት ላሳዩት አጋርነት እና አብሮነት አክብሮታቸውን እና የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

ድሬዳዋ አስተዳደር “ትንሿ ኢትዮጵያ” የአብሮነትና የፍቅር ከተማ!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *