በስነስርዓቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር የአከባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ አባመጋል እንደገለፁት :መሬት እንዲያገግም በማድረግ በረሃማነትና ድርቅን በመቋቋም የተራቆቱ ቦታዎችን በማልማት ከተረጂነት መላቀቅ እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አካባቢን መንከባከብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል ።
የተጎዱ አከባቢዎችን በልዩ ሁኔታ እንዲያገግም በማድረግ ከድርቅ ስጋትና ከድህነት መውጣት እንደሚቻል በዚሁ ወቅት ተገልጿል ።
የምግብ ዋስትናን ለማረገጋጥ የሚቻለው ለአከባቢያችን ጥበቃና እንክብካቤ ሲደረግለት እንደሆነ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ድሬዳዋ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማትን የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል።
የአለም የአከባቢ ቀን ዘንድሮ እንደዓለም ለ51ኛ ግዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ31ኛ ግዜ ተከብሯል።
ቀኑን አስመልክቶ በድሬዳዋ በሐረላ ገጠር ቀበሌ የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ጆግራፊ ክፍል ተማሪዎችና የሃርላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ማህበረሰቡ የተሳተፈበት ችግኝ የመንከባከብና ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር ተከናውኗል።


