ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር ለዲያስፖራ የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

በድሬደዋ አስተዳደር በንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ተቋማት ለዲያስፎራ የሚሰጡትን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከዲያስፖራ ፎካል ፐርሰን ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ::

በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የቅድሚያ ኢንቨስትመንት መስክ እና መሬት በማቅረብ እና በማልማት የተሻለ የካፒታል አቅም ያላቸው ዲያስፖራዎችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሳተፉ ለማስቻል እና የቤቶች ልማት አማራጮች በማሳተፍ በሀገራቸው ቋሚ ንብረት እንዲኖራቸው እና ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጻል::

የድሬዳዋ አስተዳደር የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ግርማ በመድረኩ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ዲያስፖራዎች በኢንቨስትመት ዘርፍ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን የእውቀትና የክህሎት ሽግግር እና የዜጎቻችን የስራ እድል ፈጣሪዎች እንደመሆናቸው መጠን በየተቋሞቻችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ በየተቋማት ከሚገኙ የዲያስፖራ ፎካል ፐርሰን ጋር በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል::

በመድረኩ ላይም ለዲያስፖራዎች ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *