በድሬዳዋ አስተዳደር ሀገራዊ የምክክር መድረክ በዛሬው ውሎ ባለድርሻ አካላት በቡድን ያደራጁትን የተጠቃለለ አጃንዳቸውን አቅርበዋል ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በዛሬው የአምስተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማህበራትና ተቋማት፣ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና የታዋቂ ግለሰቦች ወኪሎች ተወያይተው የተስማሙባቸውን አጀንዳዎች በመረጧቸው የቡድን መሪዎች አማካኝነት ለጋራ መድረኩ አቅርበዋል::

ከባለድርሻ አካላት የተመረጡ ወኪሎች ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተሰበሰቡ የድሬዳዋ አስተዳደር አጀንዳዎችን አደራጅተውና አጠናቅረው በጋራ መድረኩ ካቀረቡ በኋላ በቀጣይ ጊዜያት ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *