በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር አሌክሲስ ላሜክ የተመራ የልኡካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ድሬዳዋ ገብቷል

#DGC መስከረም 10/2017

አምስት የተለያዩ የፈረንሳይ ሴናተሮችን ያካተተው እና በሚስተር ሀውገስ ሳውሪ የቡድን ፕሬዚዳንትነት እየተመራ ድሬዳዋ አለማቀፍ አየር ማረፊያ የደረሰውን የፈረንሳይ አምባሳደር በአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የልኡካን ቡድኑ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚኖረው ቆይታው የቱሪዝም መስህቦችን ታሪካዊ ቦታዎችን የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንደሚጎበኝ የወጣው መርሃ ግብር ያመላክታል ።

ከሁለት ሳምንት በፊት የሹመት ደብዳቤያቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በይፋ ስራ የጀመሩት የፈረንሳይ አምባስር አሌክሲስ ላሜክ የመጀመሪያ የይፋዊ የሥራ ጉብኝቴን ከሶስት የፈረንሳ ሴናተሮች ጋር በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ማድረጌ የሁለቱ ሀገራት ጥብቅ ዲፕሎማሲዊና ታሪካዊ ወዳጅነት መነሾ ድሬዳዋ በመሆኗ ነው ያሉ ሲሆን ይህኑን ግንኑነት ወደ ላቀ ምእራፍ ለማሳደግ በማለም ነው ብለዋል::

የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ አመት አስመልክቶ የሚደረገው ይሔ ጉብኝት በድሬዳዋ ከተማ መደረጉ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙኘት በተጀመረ ሶስት አመታት በኋላ በፈረንሳይ መሐንዲሶች ጉልህ አሻራ በተቆረቆረችውና የ122 አመታት እድሜ ባለቤት በሆነችው ድሬዳዋ መደረጉ ትርጉሙን የጎላ የሚያደርገው እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር ታህሳስ 24 ቀን 19 02 ዓ/ም ድሬዳዋ ከተማ ከደረሰው የመጀመሪያው ባቡር ዳና እኩል የሚቆጠር በመሆኑ ነው ተብሏል።

በዳንኤል አማረ

ፎቶ:- አብይ ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *