#DGC | ህዳር 2 / 2017 ዓ.ም
በዛሬው ዕለት ማለትም ህዳር 2/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የተመራው ልዑክ እና የአስተዳድሩ ከፍተኛ አመራሮችም በተገኙበት በወረዳ 03 እና በወረዳ 07 በክረምት የበጉ ፍቃድ ስራ የተሰሩ የአረጋውያን ቤት በአዲስ መልክ በመስራት ዛሬ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ቤቱን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል ።
የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እና ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም የሚመች ሀገር የመገንባት እና ሁሉም ዜጋ የተሻለ ኑሮ የሚኖርበትን መልካም ሁኔታ ለዜጎች የሚያመቻች መሆኑን በመግለፅ በድሬዳዋ አስተዳድርም የፓርቲው 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ሲከበር ባለፉት ዓመታት የህዝቡን ችግር ለመፍታት የተከናውኑ ተግባራትን በማስታወስና በአፈፃፀም ሂደት የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የታሰበ እንደሆነ ተገልፀዋል።
በዚህም በ03 ወረዳ 2 ቤቶች እና በ07 ወረዳ ደግሞ 3 ቤቶች በአዲስ መልክ ተገንብተው የተሰሩ ሲሆን ቤቶቻቸውን የተረከቡት አረጋውያንም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምስል፡ አገኘው ሸዋረጋ


