የድሬ አዋርድ በዛሬው እለት ተካሄደ ። ስኬታማ ግለሰቦችና ተቋማትን የሚሸልመው የድሬ አዋርድ በዛሬው እለት ተካሂዷል ።

#DGC | ህዳር 7 / 2017 ዓ.ም

በዚሁ የድሬ አዋርድ የሽልማት መርሀ-ግብር ላይም በበጎ-ሰው ዘርፍ ፣ በንግድ ዘርፍ ፣ በትምህርት ዘርፍ ፣ በህክምና ዘርፍ ፣ በጥበብ ዘርፍ ፣ በስፖርት ዘርፍ ፣ በመንግስታዊ የስራ ሀላፊነት ዘርፍ እንዲሁም የአመቱ አጠቃላይ ተሸላሚ ዘርፎች አሸናፊ ለሆኑ አካላት ሽልማት ተበርክቷል ።

በድሬ አዋርድ መርሀ-ግብር ላይም የአመቱ ምርጥ ተሸላሚ የሆኑት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በተለይም የመረጣቸውን ማህበረሰብ በታማኝነት እና በቅንነት ከማገልገል በዘለለ በአስተዳደሩ ላይ መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረው የድሬ አዋርድ አዘጋጆች እንዲሁም ለመርሀ-ግብሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱትን አመስግነዋል ።

የድሬ አዋርድን በየአመቱ በማዘጋጀት ከመመሰጋገን ጎን ለጎን በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ በፖለቲካ ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በኢኮኖሚው መስክ እየተሰሩ ያሉትን አጠቃላይ ስራዎች ለማስቀጠል በእጅጉ እንደሚያግዝ የድሬ አዋርድ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ወገን ወሰን ተናግረው የድሬ አዋርድ መርሀ-ግብር እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋናውን በእለቱ አቅርቧል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ

+17

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *