17ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ቀን በድምቀት ተከበረ

#DGC ህዳር 22/2017

“የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለፈጠራ ክህሎት” በሚል መሪ ቃል 17ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል። በክብረ በአሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የኮሚሽነር ተወከይና የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ባህር አብደላ ናቸው፡፡

አቶ ባህር ወጣት እምቅ ሀብት ነው ያሉ ሲሆን የአንድ ሀገር መፃኢ ዕድል ያለው ወይም የሚረጋገጠው አውንታዊ ሚናን መጫወት በሚችል ወጣት ትውልድ ነው፡፡ ወጣትነት በትኩስ ሀይል በእምቅ ጉልበት፤ በአዕምሮ ብቃት የታጀበ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ይህን ወጣት በብዙ ሀይልና ግፊት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአግባቡ መያዝ፤ መግፋትና መጠቀም ለብልፅግና ህልምና ስኬት ብቻ ሳይሆነን ለኢትዮጲያ ፈጣን እድገት መሠረት ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በወጣቶች ዘርፍ ፖሊሲ ቀርፆ በየደረጃው ባሉ ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ተፈጻሚ በማድረግ የተለያዩ ስራዎች በየደረጃው እየተሰራበት ይገኛል፡፡ የድሬዳዋ አሰተዳደርም ወጣቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድልና ሁኔታዎች በማመቻቸት አጫጭር የሞያና የፈጠራ ክህሎት ስልጠናዎች በተጨማሪ ወጣቱን ቴክኖሎጂ ባሏቸው አቅምና ችሎታ እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራ በትኩረት መሰራቱን አቶ ባህር ተናግረዋል፡፡

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለከተማችን ብልፅግና ብሎም ለሀገራችን የእድገት ብልፅግና ያለው አስተዋፅኦ አንፃር ትኩረት ሰጥቶ መስራት አስፈላጊነቱን መነሻ በማድረግ ወጣቱን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ንቅናቄ እና ግንዛቤ በመፍጠር አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኩነቶችን በዛሬው እለት እያከበርን እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮን የአፍሪካ ወጣቶች ወር በአፍሪካ ደረጃ Educate And Skill Africa For The 21 centure በሚል መሪ ቃል ለ18ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ የተቀየረው የወጣቶች የስራ ባህል ለፈጠራ ክህሎት በሚል መሪ ቃል ለ17ኛ ጊዜ መከበሩን የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተወከይና የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ባህር አብደላ አብራርተዋል፡፡

በ17ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ቀን ፕሮግራም ላይ የአስተዳደሩ ስኬታማ ወጣቶች የስራ ፈጠራቸውን ለታዳሚዎች ያቀረቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዲጂታል የህክምና መገልገያ ማሽን፣ የውሃ ፓንፕ መስሪያ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ማሽን፣ እንዲሁም ከወዳደቁ ጨርቆች የተሰራ የፈጠራ ልብስ ውጤቶች ቀርበዋል፡፡

በበድሉ ሀይሌ

ምስል፡- ሙላለም ደሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *