በስራ ዕድል ፈጠራ በኩል የሚሰሩ ስራዎች የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እውን የሚያደርጉ መሆን እንደሚገባቸው ተገለፀ

#ህዳር 23/2017

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ በድሬዳዋ አስተዳደር በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በወረዳ 08 እና 09 የተቷገበሩና የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተኙ ውጤቶች የተመለከቱ ሲሆን ከተጠቃሚዎች ጋር እና ከዘርፉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ዳንኤል ድሬዳዋ የተገኙበት ዋና አላማ እንደ ሀገር በስራ ዕድል ፈጠራ በኩል የሚሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ረገድ የታሰበላቸውን ውጤት እንዲያስገኙ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ መሆኑን ገልፀው በጉብኝታቸውም በከተማዋ በስራ ዕድል ፈጠራ በኩል የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንዳለ የሚያመላክት ነዉ ብለዋል።

በቀጣይ በአስተዳደሩ በሚኖራቸው ቆይታም እንደ ስራ ክህሎት ሚኒስቴር በተቀመጡ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች መሠረት ማለትም የተቋማት ግንባታ፣ የክህሎት ልማት፣የስራ ዕድል ፈጠራ፣የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይና የኢንዱስትሪ ሰላማዊ ግንኙነት በአስተዳደሩ በምን አይነት ሁኔታ እየተጓዘ እንዳለ ቅኝት እንደሚያደርጉ ሚኒስቴር ዲኤታው ገልጸዋል።

አቶ ዳንኤል አክለውም በድሬደዋ የተመለከቷቸውን የስራ እድል ፈጠራ እንደ ሀገር ሚናቸው የላቀ እንዲሆን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራና፥ ብሎም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ነው ያረጋገጡት።

የመስክ ጉብኝቱ ነገም ቀጥሎ መሰል ስራዎች ላይ ጉብኝትና ግምገማ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ፎቶ፦አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *