የአርቲስት መሃዲ ሼካ <<ቶኩማ>> የተሰኘው 14ተኛ አልበም ተመረቀ።

በመረዋ ድምፁ እና ገዥ በሆነው የመድረክ አያያዙ፤ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለው ስለ ኦሮሞ ጥበብ እና ባህል በሙዚቃዎቹ ያስተዋወቀው አርቲስት መሃዲ ሼካ በዛሬው እለት 14ተኛ አልበሙን በድሬዳዋ አስተዳደር አስመረቀ::

ከዚህ ቀደም 13 አልበሞችን ለአድናቂዎቹ ያበረከተውና በተለይም <<መንኢ አባ ገዳ>> በሚለው ዘፈኑ በብዙዎች ዘንድ የሚታውቀው አርቲስት መሃዲ ሼካ <<ቶኩማ>> የተሰኘው 14ተኛ አልበሙን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የሙያ አጋሮቹ፣ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር በተገኙበት በቢ ካፒታል ሆቴል በድምቀት አስመርቋል።

በሙዚቃ አልበም ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር ድሬዳዋ ብዙ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ያፈራች ከተማ መሆኗን ገልፀው፤ ከነዚህም መሃል መሃዲ ሼካ አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

ስለ ኦሮሞ ባህል እና ጥበብ በሙዚቃዎቹ ያስተዋወቀ አርቲስት እንደሆነ ገልፀው <<ቶኩማ>> አልበምን አስተዳደራችን ላይ ለማስመረቅ በመምረጡ አመስግነዋል።

ክቡር ከንቲባ ከድር አክለውም ስለ አንድነት የሚያቀነቅነው <<ቶኩማ>> አልበም አንድንታችን እና ሰላማችን በተመሰከረበት ይበልጥ ለማስቀጠል በምንሰራበት በዚህ ወቅት መመረቁ አልበሙን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል::

በበድሉ ሀይሌ

ምስል፦ አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *